አብካዝያ
Appearance
አብካዝያ (አብካዝኛ፦ /ኣጵስንይ/) በከፊል ተቀባይነት ያገኘ አገር ነው። ነጻነቱን በ1984 ዓ.ም. ያዋጀ ምንም ቢሆን፣ ጂዮርጂያ ግን ይግባኝ አለው።
ከተባበሩት መንግሥታት የሚከተሉት አገራት አብካዝያን ተቀባይነት ሰጥተዋል፦ ሩስያ፣ ኒካራጓ (በ2000 ዓ.ም.) ፤ ቬኔዝዌላ (2001 ዓ.ም.)፣ ናውሩ (2002 ዓ.ም.)፣ ሶርያ (2010 ዓ.ም.)።
በከፊል ተቀባይነት ካገኙት ሌሎች አገሮች፣ ደቡብ ኦሤትያ-አላኒያ፣ ትራንስኒስትሪያ እና አርጻኽ አብካዝያን እርስ በርስ ይቀበላሉ።
በተጨማሪ ቫኑአቱ ከ2003 እስከ 2005 ዓ.ም. ድረስ አብካዝያን ይቀበል ነበር። እንዲሁም ቱቫሉ ከ2003 እስከ 2006 ዓ.ም. ድረስ ይቀበለው ነበር።
የተረፉት መንግሥታት የጂዮርጂያ ግዛት እንዲሆን የጂዮርጂያን ይግባኝ ተቀባዮች ናቸው።
|