Jump to content

ሳዑዲ አረቢያ

ከውክፔዲያ

የሳኡዲ አረቢያ ግዛት

የሳዑዲ አረቢያ ሰንደቅ ዓላማ የሳዑዲ አረቢያ አርማ
ሰንደቅ ዓላማ አርማ
የሳዑዲ አረቢያመገኛ
የሳዑዲ አረቢያመገኛ
ሳኡዲ አረቢያ በአረንጓዴ ቀለም
ዋና ከተማ ሪያድ
ብሔራዊ ቋንቋዎች አረብኛ
መንግሥት
{{{ንጉስ
 
ሳልማን ቢን አብደል አዚዝ
የመሬት ስፋት
አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.)
ውሀ (%)
 
2,149,690 ኪ.ሜ. (14ኛ)
የተተወ
የሕዝብ ብዛት
የእ.አ.አ. በ2017 ግምት
 
33,000,000 (41ኛ)
ገንዘብ የሳዑዲ ሪያል
ሰዓት ክልል UTC +3
የስልክ መግቢያ 966


ሣውዲ አረቢያ ግዛት 28.7 ሚሊዬን የሚሆን ህዝብ ብዛት የያዘ ሲሆን 2ዐ ሚሊዬኑ የሣውዲ ዜጎች ሲሆኑ 8 ሚሊዬኑ የሌላ አገር ዜጎች ናቸው፡፡

ሳውዲ አረቢያ በምዕራብ ኤዥያ ከሚገኙ አገሮች በሙሉ በቆዳ ስፋቷ አንደኛ ናት፡፡ የአገሪቱ መሬት ስፋት 2,15ዐ,ዐዐዐ ኪሎ ሜትር ስኩኤር ነው፡፡ ጆርዳን እና ኢራቅ በሰሜን፣ ኩዌት ደግሞ በሰሜን ምስራቅ ኳታር ባህሬን እና የዩናይትድ አረብ ኤምሬት በምስራቅ ኦማን በደቡብ ምስራቅ እና በስተመጨረሻ የመን በደቡብ በኩል ሣውዲ አረቢያ ያዋስኗታል፡፡ የቀይ ባህር እና የፐርዢያን ገልፍ ባህርን የያዘ ብቸኛ አገር ሲሆን የሣውዲ መሬት ለመኖር በሚያስቸግር በረሃ የተከበበ ነው፡፡

የሳዑዲ ግዛት መስፋፋት ከ1906 እስከ 1926 ዓም ድረስ።

አሁን ያለው የሣውዲ ግዛት በፊት ጊዜ አራት ቦታዎችን ያጠቃለለ ነበር፡፡ ሄጃዝናጅድአል አሻ እና አስርን የያዘነው፡፡ የሣውዲ አረቢያ ግዛት ተመሠረተው በ1932 እ.ኤ.አ. በኢብን ሣኡድ በተባለ ሰው ነው፡፡ ኢብን ሣኡድ ቀድሞ በ1894 ዓም (1902 እ.ኤ.አ.) ከብሪታንያ ግዛት ከኩወይት ዘምቶ ሪያድን ያዘ። ኢብን ሳኡድ አራት የነበሩትን የተለያዩ ግዛቶች አንድ በማድረግ ሣውዲ አረብያን ከተመሠረተ ጀምሮ እስከአሁን ድረስ ሀገሪቱ በዘውድ አገዛዝ እና በእስልምና ሃይማኖት መሠረት እየተዳደረች ትገኛለች፡፡ እስልምና ሃይማኖትን በተመለከተ ዋሀቢ እስላም የሣውዲ አረቢያ አንደኛ እምነት ነው ተብሎ ይታሰባል፡፡ ለእስልምና እምነት ትልቅ ቦታ የሚይዙት ቅዱስ ስፍራ ተብለው መካ እና መዲና በሣውዲ ስለሚገኙ ሣውዲ አረቢያ አብዛኛው ጊዜ የተቀደሱትን ሁለት መስጊዶች የያዘው መሬት ተብሎ ይታወቃል፡፡

ሣውዲ አረቢያ በዓለም ላይ ካሉ ትልቅ የነዳጅ አምራች ሀገራት ሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ በተጨማሪም ሣውዲ አረቢያ በዓለም ላይ ካሉ ሀይድሮ ካርቦን ክምችት ካላቸው አገሮች በሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ በሀገሪቱ ባለው የተፈጥሮ ሀብት ከፍተኛ ክምችት ምክንያት ከፍተኛ የኢኮኖሚ ገቢ እና የህዝብ ቁጥር እድገት ከያዙ ሀገራት ጋር ትመደባለች፡፡ ሣውዲ አረቢያ G-2ዐ ተብለው ከሚታወቁት ከፍተኛ የኢኮኖሚ አቅም ካላቸው የሀገራት ቡድን ውስጥ ብቸኛዋ የአረቡ ዓለም አገር ናት፡፡ ይህም ቢሆን የሣውዲ ኢኮኖሚ በአብዛኛው በአንድ ቡድን የተያዘ ነው፡፡ የሣውዲ አረብያን ፈላጭ ቆራጭ በሆነ የመንግስት ስርዓት በመመራት “ነጻነት የለም” በሚል “ነጻነት ቤት” በሚል በሚታወቀው ድርጅት ተሰይማለች፡፡

ሣውዲ አረቢያ በዓለም ላይ ለጦር ሀይል ከፍተኛ ገንዘብ ከሚያወጡ አገሮች ዝርዝር በአራተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ እ.ኤ.አ. ከ2ዐ1ዐ-2ዐ14 በስኘሪ ተብሎ በሚታወቅ ድርጅት በተደረገው ጥናት ሣውዲ አረቢያ ዓለም ላይ ከሚገኙ የጦር መሣሪያዎች በከፍተኛ ደረጃ በማስገባት ሁለተኛዋ ሀገር ናት፡፡ ሣውዲ አረቢያ በአካባቢው ካሉ ሀገሮች በዓለም ላይ ከፍተኛ አስተዋጾኦ በማድረግ ላይ ያለች አገር ናት፡፡ የኦፔክጂሲስ እና የእስላም ግሩፕ አባል ናት፡፡