ቀስተ ደመና
Appearance
የከባቢያችን አየር ያዘለው የውሃ ትነት ከፀሐይ የሚመጣውን ነጭ ብርሃን በመበተን ወደ ህብረ ቀለማት ሲቀይረው ያን ጊዜ ቀስተ ደመና ይባላል። ብዙን ጊዜ ቀስተ ደመና የግማሽ ክብ ቅርጽ ሲይዝ የክቡ የውጭኛው ክፍል ቀለም ቀይ ሲሆን የውስጠኛው ክፍል ደግሞ ወይን ጠጅ ነው።
በርግጥ ቀስተ ደመና ወጥ የሆነ ህብረ ቀለም ቢሆንም ላይናችን ግን የተከፋፈለና የተለያዩ የቀለም አይነቶች በክብ መስመር ያሉበት ይመስለናል። ቀስተ ደመና በምን አይነት ሂደት በአየር ላይ በተንጠለጠሉ የውሃ ጤዛዎች እንደሚሰራ አረቡ አል ሃይታም ከዚያም በኋላ የፈረንሳዩ ደካርት አጥጋቢና ትክክል ምክንያት ሰጥተዋል።
በነገራችን ላይ ፀሃይ ምንጊዜም ከቀስተ ደመና ፊት ለፊት እንጂ ከሁዋላ አትገኝም።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ደግሞ ቀስተደመና በእግዚአብሔር እና በኖኅ መካከል የቃል ኪዳን ምልክት ነው፡፡ (ምሳሌነቱም ለድንግል ማርያም ተሰጥቷል)
ስለዚህም ቀስተደመና ሲታይ ክርስቲያኖች ደስ ይላቸዋል፡፡ ከእግዚአብሔር የተሰጠ የእርቅ ምልክት ተደርጎ ይቆጠራልና፡፡ በስምም "የማርያም መቀነት" ተብሎ ይጠራል!