Jump to content

ላዛኛ

ከውክፔዲያ

አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
  • ግማሽ ኪሎ ግራም ቤት የተዘጋጀ ወይም ታሽጐ የሚሸጥ ላዛኛ
  • 5 ትልልቅ እንቁላል
  • 5 መካከለኛ ጭልፋ ቦሎኔዝ ሶስ
  • 8 የሾርባ ማንኪያ (200 ግራም) የገበታ ቅቤ
  • 5 መካከለኛ ጭልፋ ቢሻሜል ሶስ
  • 1 የሾርባ ማንኪያ ዘይት
  • 1 የሻይ ማንኪያ ጨው
  • 2 መካከለኛ ጭልፋ (200 ግራም) የተፈጨ ቺዝ
  • 1. ጨው፣ ዘይትና በርከት ያለ ውሃ አፍልቶ ላዛኛውን እየዘረጉ መጨመር፣
  • 2. ለአምስት ደቂቃ ካበሰሉ በኋላ እንዳይሰባበር ወይም እንዳይቦካ በጥንቃቄ አውጥቶ ቀዝቃዛ ውሃ ያለበት ሰፋ ያለ ዕቃ ውስጥ መጨመር፣
  • 3. እንዳይሰባበር ተጠንቅቆ አውጥቶ በንፁህ አቡጀዲ ላይ አድርጐ ጫን፣ ጫን እያደረጉ መጠጥ እንዲል ማድረግ፤
  • 4. የዳቦ መጋገሪያ ትሪ ላይ ሁለት የሾርባ ማንኪያ ቅቤ መቀባት፤
  • 5. ትሪው ላይ ላዛኛውን በነጠላው ከዳር እስከዳር ማንጠፍ፤
  • 6. የሥጋ ሶሱንና እንቁላሉን ደባልቆ መምታት፤
  • 7. ከውሁዱ 2 መካከለኛ ጭልፋ አውጥቶ የተነጠፈው ላዛኛ ላይ በተመጣጠነ መልኩ መቀባት፤
  • 8. ሁለት መካከለኛ ጭልፋ ቢሻሜል ሶስ ከላዩ ጨምሮ ማዳረስ፤
  • 9. በዚህ ዓይነት አንድ ተጨማሪ ድርብ መጨመር፤
  • 10. ከላዩ ላዛኛ በማንጠፍ ከዳር እስከ ዳር መሸፈን፣
  • 11. መጀመሪያ ቀሪውን ውሁድ፣ ቀጥሎም የቀረውን ቢሻሜል ጨምሮ መቀባት፤
  • 12. ቺዙን ከዳር እስከዳር መነስነስና ቅቤ አልፎ፣ አልፎ ጣል ጣል ማድረግ፤

13. ወርቃማ መልክ እስከሚያወጣ ፉርኖ ቤት ወይም የዳቦ መጋገሪያ ውስጥ ማብሰል።

[ከዚህ በተለየ መጀመሪያ ቢሻሜል ሶሱን፣ ቦሎኔዝ ሶሱንና እንቁላሉን አዋህዶ በየደረጃው ውህዱን ከላይ በተጠቀሰው መልኩ በመቀባት ማዘጋጀት ይቻላል።]