Jump to content

ላፓዝ

ከውክፔዲያ

ላፓዝ (La Paz) የቦሊቪያ ዋና ከተማ ነው።

መሀል ላፓዝ

የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር (1997 ዓ.ም.) 1,250,000 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 16°30′ ደቡብ ኬክሮስ እና 68°10′ ምዕራብ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።

የጥንቱ ኗሪዎች በሥፍራው ቹቂያፑ (ማለት 'የወርቅ እርሻ' በቀቿ) የተባለ መንደር ነበራቸው። ከተማው ንዌስትራ ሴኞራ ዴ ላ ፓዝ (እስፓንኛ፣ 'የሰላም እመቤታችን') ተብሎ በስፓኒሾች1541 ዓ.ም. ተሠራ። በ1817 ዓ.ም. ከአያኩቾ ውግያፔሩ ቀጥሎ፣ ስሙ ላፓዝ ዴ አያኩቾ ('የአያኩቾ ሰላም') ተደረገ።

1890 ዓ.ም. የመንግሥት መቀመጫ ከሱክሬ ወደ ላፓዝ ተዛወረ። ይሁንና በሕጋዊ ረገድ (በስም ብቻ) ሱክሬ እስከ ዛሬ ድረስ ዋና ከተማነቱን ይዟል።