Jump to content

ዕዝራ

ከውክፔዲያ

ዕዝራ (ዕብራይስጥ: עֶזְרָא) ወይም ሱቱኤልመጽሐፈ ዕዝራ ምዕ. 7 በብሉይ ኪዳን ዘንድ በባቢሎን ምርኮ ጊዜ የአይሁድ ካህን ነበረ። የሠራያ ልጅ ሲሆን በፋርስ ንጉስ አርጤክስስ 7ኛው አመት (464 ክ.በ.) ከ5000 ከወገኖቹ ጋራ ወደ ኢየሩሳሌም ለመመለስ ፈቃድ ተቀበለ።

ከዚህ 13 አመት በኋላ ነህምያ የከተማውን ቅጥር ሲጠግነው ዕዝራ ኦሪት በሙሉ ለሕዝብ አነበበ (መጽሐፈ ነህምያ ምዕ. 8)።

በአይሁዳዊው ታሪክ ጸሐፊ በዮሴፉስ ዘንድ ይህ የፋርስ ንጉስ አርጤክስስ ሳይሆን አሕሻዊሮስ ነበረ። አርጤክስስ የአሕሻዊሮስ ልጅ ሲሆን እነዚህ 2 ነገስታት ስሞች ብዙ ጊዜ በተለያዩ ቅጂዎች ተደናገሩ። ዮሴፉስ ደግሞ ዕዝራ የሞተበት ወራት ኤልያሴብ ታላቁ ካህን በሆኑበት ወቅት ገደማ እንደ ነበር ይመሰክራል። የአሕሻዊሮስ ዘመን ከሆነ 7ኛው አመት 486 ክ.በ. ነበር።

ዕዝራ መጽሐፈ ዕዝራንና መጽሐፈ ነህምያ ከመጻፉ በላይ በዲዩትሮካኖኒካል መጽሐፍት ክፍል የሚገኙት መጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤልመጽሐፈ ዕዝራ ካልዕ እንደ ጻፈ ይባላል። መጽሐፈ ዕዝራ ካልዕ ለመጽሐፈ ዕዝራ በጣም ተመሳሳይ በመሆኑ በዕዝራ ካልዕ 8:1 ግን ሠራያ ሳይል በግድፈት የአዛርያስ ልጅ ይለዋል። ዕዝራ ሱቱኤል በሚባለው ትንቢት ደግሞ በ1:1 የጻፈው ኢየሩሳሌም ከጠፋች 30 አመት በባቢሎን መሆኑን ይላል። ይህም 565 ክ.በ. ማለት ነው። በዚህ መጽሐፍ 13:44 መሠረት 24 መጻሕፍት በ40 ቀን ውስጥ ጻፈ ቢለን፥ በሌሎች ልሣናት ሕትመት ግን ስለ 94 መጻሕፍት እየተናገረ ከነዚህ መሀል ተጨማሪው 70 መጻሕፍት በምስጢር እንዲቆዩ ነበረባቸው ይላል።

እስልምና የዕዝራ ስም ደግሞ በቁርዓን ውስጥ (9:30) 'ዑዛዒር' ተብሎ ሲጻፍ ይገኛል። አይሁዶች ዑዛኢርን የእግዚአብሔር ልጅ በመሳሳት እንዳሉት ይላል።

መጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤልዲዩተሮካኖኒካል ወይም አዋልድ መጻሕፍት ተቆጥሮ የሱቱኤል ትንቢት ነው።